አባልነት
ለማናቸውም ቀናተኛ ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ቀድሞ በአንድ ጠንካራ የማህበር ጥላ ስር መዋቀሩን መርጠን ባለን ችሮታ ሁሉ ዕውን ለማድረግ ስንጥር፤ በኮሚኒቲ ዓባልነቴ ማኅበሩ ከእኔ ምን ይፈልግ ይሆን? ከምንስ ልጀምር? ብለው ለሚያስቡ ሁሉ የመጀመሪያውን ደረጃ የዓባልነትን ማስመስከሪያ ተግባር
«ተመዝግቦ ወርዓዊ መዋጮን በመክፈል» ህሊናን ነጻ ማድረግ በጎ እርምጃ ነው ብለን እናምናለን። ብናደርገው በተለይ ከሚጠይቀው የመስዋዕትነት ዘቅተኝነት አንጻር ሲታይ፤ ግን ደግሞ ከአንድ ብርቱ ነውና ከብዛት ከሚገኘው የህብረት ውጤት ስኬታማነቱ አመርቂ ይሆንልናልም።
እርስዎም በእዚህ ቀና አስተሳሰብዎ ግፊት ኮሚኒቲዎን ለማጎልበት እራስዎን በመጠየቅ
ዝግጁነትዎን በማመናችን፤ እኛም በይበልጥ እንዳናገለግል ሀይል ሆኖን በቁጥር
አለማነሳችንን በውጤት ለመስመስከር ከባድ አይሆንም ለማስመስከር ከባድ አይሆንም ብለን እናስባለን። ለማናቸውም ተግባራዊ አስተዋፅዎት እናመሰግናለን።
|